የኮሚሽነር መልዕክት

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን መልዕክት

           ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ

ሙስና የሀገርን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አውድን የሚያናጋ የሀገርን ህልውና ለአደጋ የሚያጋልጥና ግለሰብን፣ ቤተሰብን፣ ተቋማትን የሚጎዳ አደገኛ ጠላት በመሆኑ በጋራ ለመከላከል ኮሚሽኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።ሙስናና ብልሹ አሰራር በሀገር ላይ የሚፈጥረው ጉዳት  አስቀድሞ ለመከላከል በሥነምግባር የታነፀ ትውልድ መገንባት እንደሚገባ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

ተቋማት ቴክኖሎጂን ተጠቅመው  አሰራራቸውን  በማዘመን ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለው እና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በዓሉ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል።በበዓሉ ሙስና አስመልክቶ ጥናታዊ ጽሁፎች የሚቀርቡ ሲሆን ህብረተሰቡ የሚያስተምሩና የሚያነቃቁ መልዕክቶች እንደሚተላለፉ ጠቁመዋል።የበዓሉ ተሳታፊዎች ወደ ተቋሞቻቸው ሲመለሱ አሰራሮቻቸው መፈተሽና ለቀጣይ ስራ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።በተለይም የሚዲያ ተቋማት በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች በመለየት ለህዝቡ ይፋ በማድረግ ሚናቸው ሊወጡ ይገባል።በአለም ለ22ኛ፣ በሀገራችን ለ21 እንዲሁም በክልላችን ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረው አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በሁሉም ትምህርት ቤቶች እና በየመዋቅሩ በሚገኙ  የመንግስት ተቋማት እና በክልሉ የክላስተር ከተሞች በተለያዩ ሁነቶ እየተከበረ ይገኛል ተጨማሪ ያንብቡ

የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች

ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ 

ዋና ኮሚሽነር
ም/ኮሚሽነር ኑሪ ከዲር 

የስነ-ምግባር ትምህርት ስልጠናና አውታሮች ማስተባበሪያ ዘርፍ ኃላፊ
ም/ኮሚሽነር ፋሲካ ጌታቸው  
የሙስናና ብልሹ አሰራር መከላከል ዘርፍ ኃላፊ

 

ኮሚሽኑ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች

የሙስና መከላከል እና አስቀድሞ ማወቅ
በስነ-ምግባር የታነጸ ዜጋ መፍጠር
ስልታዊ አመራር

የኮሚሽኑ ራዕይ ተልዕኮና አላማ

ራዕይ 
በ2022 ሙስናና ብልሹ አሰራር ለክልላችን ብልጽግና እንቅፋት እንዳይሆን በማድረግ በአገራችን ካሉት የፀረ-ሙስና ተቋማት ግንባር ቀደም ተቋም ሆኖ ማየት!                                                                                                                                                                                                                                                                       
ተልዕኮ 
ጠንካራ እና ኃላፊነቱን በብቃት ሊወጣ የሚችል ተቋማዊ አደረጃጀት በመፍጠር፣ ሙስናን ለመከላከል የሚያስችል የሥነምግባር አስተምህሮዎችን በማስተማር፣ በጥናት ላይ የተመሠረተ የቅድመ ሙስና መከላከል ሥራዎችን በመሥራት፣ በህጉ መሠረት የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ሥራዎችን በብቃት በመፈፀም እና ከሌሎች የባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት ውጤታማነትን ማረጋገጥ!
አላማ 
የመልካም ሥነ-ምግባር ተምሳሌት መሆን፤በጋራ መሥራት፤ለቀጣይ ለውጥ ዝግጁ መሆን፤የተግባር ሰው መሆን፤                                                                                                                                                                                                                                                                                                                   

ዜና

በግብርና ሴክተር እየተሰሩ ያሉ የሥነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥራ ያለበትን በመስክ ድጋፍና ክትትል ተደርጓል ።
የሁልባራግ ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤት ለትምህርት አመራሮችና የጽ/ቤት ባለሙያዎች በተለያዩ ርዕሶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ
"ትውልድን በስነ ምግባር ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የዘንድሮው 22ኛው አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን ክልላዊ በዓል አከባበር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በወራቤ ከተማ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከረ ነው።
22ኛውን አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ክልላዊ ማጠቃለያ ፕሮግራም ለማክበር ቅድ መዝግጅት ማድረጉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያክልል የሥነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ እንዲሁም አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በአል አከባበር ኦረንቴሽን ተሰጠ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው መንግስትና ፓርቲ ያቀዷቸው ትላልቅ ህልሞች እንዲሳኩ የተጠናከረ የፀረ-ሙስና ትግል መደረግ እንዳለበት አሳሰቡ።
በየደረጃው የሚደረጉ የጸረ ሙስና ትግሎች ለችግሩ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ ዘርፎች ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው ተጠቆመ። የክልሉ የፍትህ አካላት ማሰልጠኛና የህግ ምርምር ማዕከል የፍትህ ስርኣቱ መጠናከር ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመዋጋት ረገድ በሚኖረው ሚና ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።
የክልሉ ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የስነ ምግባር አውታሮች የትብብርና ቅንጅት ፎረም በአዲስ መልክ ተቋቋመ። ኮሚሽኑ የሁሉንም የመንግስት ተሿሚዎች ሀብት ማሳወቅና ምዝገባ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

 ሚዲያ

  

See More Video

አሰተያየት እና ጥቆማ መስጫ

One file only.
2 MB limit.
Allowed types: txt pdf doc docx odt pages rtf wpd wps csv numbers ods xls xlsx jpg png gif tiff webp and svg.