Skip to main content

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ እንዲሁም አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በአል አከባበር ኦረንቴሽን ተሰጠ።

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ እንዲሁም አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በአል አከባበር ኦረንቴሽን ተሰጠ። 

ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም (ቡታጅራ) 

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ለክልል ተቋማት፤ ለዞንና ለልዩ ወረዳዎች የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች የተዘጋጀ  የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ የኦረንቴሽን መድረክ በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ አካሂዷል። 

የክልሉ የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ማም ቴጋ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት ሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ልዩ ትኩረት በመስጠት ተጋላጭ በሆኑ የስራ መደቦች ላይ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል። የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዋና ዓላማ የግልፀኝነትና ተጠያቂነት ስርዓት ለማስፈን መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ ቀሪ ጊዜያት ሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የራስ ተነሳሽነት በመፍጠር ጠንካራ ስራዎች መስራት እንዳለባቸው  አስረድተዋል። 

በኦረንቴሽን መድረኩ የክልሉ የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነርና የሙስና መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፋሲካ ጌታቸው፤ የስነምግባርና ትምህርት ስልጠና አውታሮች ማስተባበሪያ ዘርፍ ኃላፊና የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር  አቶ ኑሪ ከድር፤ የኮሚሽኑ የማኔጅመት አካላት፤ የክልል ተቋማት የስነ ምግባር መከታተያ ክፍል ዳይሬክተሮች፤ የዞንና የልዩ ወረዳ የስነምግባርና ፀረ ሙስና ቡድን መሪዎች ተሳትፈውበታል። በሌላ በኩል በክልላችን ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በዓል አከባበርን በተመለከተ የማስፈፀሚያ እቅድ ላይ ኦረንቴሽን ተሰቷል። በዚህም በአሉ የሚከበርበትን ሁኔታና የቀጣይ አቅጣጫ ላይ በስፋት በመወያየት በአሉን ከወትሮው በበለጠ ድምቀት በንቅናቄ ለማክበር መግባባት የተፈጠረ ሲሆን የኦረንቴሽን መድረኩም በቀጣይ በየመዋቅሩ ቀጥሎ እንደሚካሄድ በኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ አቅጣጫ አስቀምጠው መድረኩ ተጠናቋል።

Image