Skip to main content

የኮሚሽነር መልዕክት

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን መልዕክት

           ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ

ሙስና የሀገርን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አውድን የሚያናጋ የሀገርን ህልውና ለአደጋ የሚያጋልጥና ግለሰብን፣ ቤተሰብን፣ ተቋማትን የሚጎዳ አደገኛ ጠላት በመሆኑ በጋራ ለመከላከል ኮሚሽኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።ሙስናና ብልሹ አሰራር በሀገር ላይ የሚፈጥረው ጉዳት  አስቀድሞ ለመከላከል በሥነምግባር የታነፀ ትውልድ መገንባት እንደሚገባ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

ተቋማት ቴክኖሎጂን ተጠቅመው  አሰራራቸውን  በማዘመን ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለው እና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በዓሉ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል።በበዓሉ ሙስና አስመልክቶ ጥናታዊ ጽሁፎች የሚቀርቡ ሲሆን ህብረተሰቡ የሚያስተምሩና የሚያነቃቁ መልዕክቶች እንደሚተላለፉ ጠቁመዋል።የበዓሉ ተሳታፊዎች ወደ ተቋሞቻቸው ሲመለሱ አሰራሮቻቸው መፈተሽና ለቀጣይ ስራ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።በተለይም የሚዲያ ተቋማት በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች በመለየት ለህዝቡ ይፋ በማድረግ ሚናቸው ሊወጡ ይገባል።በአለም ለ22ኛ፣ በሀገራችን ለ21 እንዲሁም በክልላችን ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረው አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በሁሉም ትምህርት ቤቶች እና በየመዋቅሩ በሚገኙ  የመንግስት ተቋማት እና በክልሉ የክላስተር ከተሞች በተለያዩ ሁነቶ እየተከበረ ይገኛል ተጨማሪ ያንብቡ