Skip to main content

የኮሚሽኑ ስልጣንና ተግባር

  • በፌደራል ደረጃ የሚወጡ የፀረ-ሙስናና የስ-ነምግባር ግንባታ ፖሊሲዎችን ያስተባብራል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣ ክልላዊ የፀረ-ሙስና ፖሊሲና ስትራቴጂ ያዘጋጃል፣ ያስፀድቃል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፤በልማታዊ ዘርፍ ተሠማርተዉ ሙስናን እና ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል ዙሪያ ከሚሰሩ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በጋራ ይሰራል፡፡
  • የክልሉን ህዝብ መልካም ሥነ-ምግባር ግንባታን እና በክልሉ መንግስት ተቋማት፣ በመንግስት ልማት ድርጅቶች እና ህዝባዊ ድርጅቶች በሚሰጧቸው አገልግሎቶች የፀረ-ሙስናና ብልሹ አሠራር ትግሉን ያስተባብራል፤
  • በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በመንግስት የልማት ድርጅቶች እና በህዝባዊ ድርጅቶች የሚሾሙ ወይም የሚመደቡ ወይም የሚቀጠሩ የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ስራ ከመጀመራቸው በፊት ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመቀናጀት የስነ ምግባር እና የሙስና መከላከል ስልጠና እንዲወስዱ ያደርጋል፤
  • በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በመንግስት የልማት ድርጅቶች እና በህዝባዊ ድርጅቶች ውሰጥ ለሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጡ እና ሊጋለጡ የሚችሉ የአሰራር ሥርዓቶችን በማጥናት ወይም እንዲጠኑ በማድረግ የመፍትሄ ሃሳቦችን ያቀርባል፣ ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል፣ ተግባራዊ ያላደረገ አካል ተጠያቂ እንዲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይሠራል፤
  • የሙስና ወንጀል ወይም ብልሹ አሰራር ለመፈፀም የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ስለመሆኑ በቂ ጥርጣሬ ሲኖረው ወይም ጥቆማ ሲደርሰው ድርጊቱ ከመፈፀሙ ወይም ከመጠናቀቁ በፊት አስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራ በመስራት ሂደቱ እንዲቋረጥ ወይም  አስፈላጊው የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ጥቆማው ለቀረበበት ተቋም ማሳሰቢያ ወይም ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፤ ወጤቱም በጽሁፍ እንዲገለፅለት ሊያዝ ይችላል፡፡
  • ከመከላከል ያለፈ ሙስና ወይም የአሠራር ሥርዓት ጥሰት ስለመፈፀሙ ወይም ተፈጽሞ ስለመጠናቀቁ በቂ ማስረጃ ሲኖረው ጉዳዩን የመመርመርና የመክሰስ ስልጣን ላለዉ አካል ያስተላልፋል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
  • የህዝብ ተመራጮችን፣ የመንግስት ተሿሚዎችን፣ ባለሥልጣናት እና የመንግስት ሠራተኞችን፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች እና የህዝባዊ ድርጅቶች የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ሃብታቸውን እንዲያሳውቁ፣ እንዲያስመዘግቡ፣ ትክክለኛነቱ እንዲረጋገጥ፣ መረጃው በአግባቡ ተደራጅቶ እንዲያዝና ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል፤
  • የሃብት ምዝገባ፣ የምዝገባ መረጃ ትክክለኛነትን ለማረጋገጥ እና የምዝገባ መረጃ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሥርዓት ይዘረጋል፤ ያስተዳድራል፣ ተመሳሳይ ቴክኖሎጂ ከሚያስተዳድሩ አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር የቴክኖሎጂ ትስስር ይፈጥራል፤ አግባብነት ያላቸው አካላት መረጃ ሲጠይቁ ከመረጃ ቋት የተደራጀውን መረጃ ይሰጣል፤
  • የሕዝብ ተመራጮች፣ የመንግስት ተሸሚዎች፣ ባለሥልጣናት የመንግስት ሠራተኞች፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች እና የሕዝባዊ ድርጅቶች የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ከተሰጣቸው ኃላፊነት፣ ከመቆጣጠር እና ከመወሰን ሥልጣን ጋር በተያያዘ የሚፈጠር የጥቅም ግጭትን ለመከላከል የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፣ ይከላከላል፣ የጥቅም ግጭት መኖሩ ሲረጋገጥ ተገቢ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ በሕግ የመመርመር እና የመክሰስ ሥልጣን ላለው አካል ያቀርባል
  • በመልካም ሥነ-ምግባር፣ ሙስናን በመታገል እና በመከላከል ረገድ በአርአያነት ውጤት ያስገኙ መስሪያ ቤቶችን፣ ድርጅቶችን፣ ግለሰቦችን እና አደረጃጀቶችን አወዳድሮ እውቅና የሚያገኙበትን እና ለሽልማት የሚበቁበትን ሥርዓትና መለኪያ ይዘረጋል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፤
  • ለህዝብ ተመራጮች፣ ለመንግስት ተሿሚዎች፣ ለመንግስት ባለስልጣናት፣ ለመንግስት ሰራተኞች፣ ለመንግስት ለህዝባዊ ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች የሚያገለግል የስነምግባር ደንብ ያዘጋጃል ወይም እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ ያስፀድቃል፣ አፈፃጸሙን ይከታተላል፤
  • ክልላዊ የሙስና ተጋላጭነት የዳሰሳ ጥናት፣ በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወይም በመንግስት የልማት ድርጅቶች ወይም በህዝባዊ ድርጅቶች ውስጥ የሙስና እና ብልሹ አሠራር ተጋላጭነት ጥናት ያካሄዳል ወይም እንዲካሄድ ያደርጋል፤ እንደ አስፈላጊነቱ የጥናቱን ውጤት ለህዝብ ይፋ ያደርጋል፣ ብልሹ አሰራር ሲኖርም እንዲስተካከል አስፈላጊዉን ክትትል ያደርጋል፤
  • በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ በህዝባዊ ድርጅቶች የስነ-ምግባር ግንባታ እና የሙስና መከላከል ተግባራትን ለመፈጸም የሚያስችሉ አደረጃጀቶችን በየደረጃው በክልሉ ዉስጥ በሚገኙ በግልና በመንግስት የትምህርት ተቋማት ያደራጃል ወይም እንዲደራጁ ያደርጋል፣
  • በክልሉ የፀረ-ሙስና ህጎች መከበራቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣ የአፈጻጸም ክፍተት ለታየበት አካል የምክር አገልግሎት ይሰጣል፣ ተገቢዉን ማስተካከያ ወይም ማስጠንቀቂያ ወይም ሁለቱንም ይሰጣል፤
  • በክልሉ ውስጥ በየደረጃው በሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በመንግስት የልማት ድርጅቶች እና በህዝባዊ ድርጅቶች ውሰጥ የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና  መከታተያ ክፍል አጥንቶ ያደራጃል ወይም እንዲደራጅ ያደርጋል፣ አስፈላጊ ሎጅስትክስ እንደተማላላቸው ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣
  • የሰዉ ሀይል ቅጥር ምደባና ስምሪትን በተመለከተ ሥርዓት ይዘረጋል፣ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ ይሰራል፣ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ  ውሳኔ ይሰጣል፤
  • የስነምግባር ትምህርትን ለማስፋፋት፣ መልካም ስነምግባርን ለመገንባትና ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል እንዲያስችለው የራሱን ሚዲያ ሊያደራጅ ይችላል፤
  • ፀረ-ሙስናና ብልሹ አሠራርን በተመለከተ የክልሉን መንግስት ያማክራል፤
  • በሙስና ወንጀል ምርመራና ክስ፣ ክስ የመስማትና የመወሰን ስልጣን ከተሰጣቸው እና ከሌሎች የፀረ-ሙስና ህጎችን ከመፈፀምና ከማስፈፀም አንፃር አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በጋራ ይሰራል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በየተቋሙ በተደራጀዉ የስነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬቶችና ቡድኖች አማካይነት ይቀበላል፣ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ግብረ መልስ ይሰጣል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
  • በአገር አቀፍ ደረጃ ስለ ፀረ-ሙስና ህጎች አፈፃጸምና አጠቃላይ የፀረ-ሙስና ትግል የሚፈለገዉን መረጃ ለፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሪፖርት ያቀርባል፣ በክልል፣ በአገር፣ በአህጉርም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚፈጠሩ መድረኮች በሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ጉዳይ መሳተፍ ሲያስፈልግ ክልሉን ወክሎ ይሳተፋል፤
  • በሥነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ጉዳይ ከሌሎች ክልሎች የሥነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽኖች ጋር በትብብር ይሰራል፤
  • በሥነ-ምግባር ግንባታ፣ በሙስና እና ብልሹ አሰራር መከላከል ተግባራትን ለማከናወን እንዲረዳው ኮሚሽኑ ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በትብብር ይሰራል፤
  • የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በራሱ ስም ይከሳል፤ ይከሰሳል፤
  • በሕግ የሚሰጡትን እና ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፤
  • የኮሚሽኑንና የሥር መዋቅር የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎችንና ሠራተኞች አስተዳደር ተግባራትን የሚያከናውን በኮሚሽኑ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የሚመራ ቡድን ይኖረዋል፡፡