Skip to main content

የሁልባራግ ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤት ለትምህርት አመራሮችና የጽ/ቤት ባለሙያዎች በተለያዩ ርዕሶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ

.....የካቲት 14/2018 ኬራቴ........

የሁልባራግ ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤት ለትምህርት አመራሮችና የጽ/ቤት ባለሙያዎች በተለያዩ ርዕሶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ

የስልጠና መድረኩን የከፈቱት የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ርድዋን ያሲን እንደገለጹት ስልጠናው ተግባራትን በብቃትና በጥራት ለመፈጸም አስፈላጊ መሆኑን አንስተው ከስልጠናው በተገኘ ግብአት ተግባራትን መፈጸም እንደሚገባ አሳስበዋል

"በጊዜ አጠቃቀም ፣በስራ ስነ-ምግባርና በስነ-ምግባር ክበብ አደረጃጀትና አወቃቀር ማኑዋል"ላይ የስልጤ ዞን የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ቡድን መሪ አቶ ረደላ ሃሚድ የግንዛቤ ማስጨበጫ የስልጠና ሰነድ ቀርቧል፡፡

እንድሁም "በተፋጠነ ት/ቤቶች ደረጃ ማሻሻያ ስትራቴጂ ፣ በአዲሱ ተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀትና አሰራር ማኑዋል እና በስኩል ግራንት በጀት አጠቃቀም መመሪያና በአካባቢ ጥበቃና ማህበራዊ ደህንነት"  የት/ቤት መሻሻል ፕሮግራም ቡድን መሪ በአቶ ትርፌ ትላንቴ አማካኝነት ስልጠናው ተሰጥቷል

በመድረኩ  ርዕሰ መምህራን ፣ሱ/ሮች እና ጽ/ቤት ባለሙያዎች ተገኝቷል ።

በመጨረሻም የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ሱልጣን አወል የስራ ስምሪት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል::

የሁልባራግ ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤት

  
Image