የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አመራሮች እና ሰራተኞች በ2017 ዓ/ም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ እንዲሁም በክልላችን አዲስ ከተዋቀረ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ለሚከበረው የአለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በዓል በተመለከተ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ያሉበት ደረጃ በዛሬው እለት ገመገመ።
ህዳር 5/2017ዓ/ም

የዘንድሮ በዓል "ሙስናን ለመዋጋት ወጣቱን ባለቤት ማድረግ፡ ነገን መገንባት "
በሚል መሪ ቃል የሚከበር ሲሆን በዓሉ ከትምህርት ቤቶች እስከ ዞን/ልዩ ወረዳ እንዲሁም በክልል ተቋማት ከህዳር 10_16/2017 ዓ/ም በልዩ ልዩ ኩነቶች በደማቅ ሁኔታ የሚከበር ሲሆን ክልላዊ የማጠቃለያ በዓሉን በተቀመጠለት መርሐ ግብር ለማክበር አብይና ንዑሳን ኮሚቴዎች በማቋቋም ወደ ስራ የተገባ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የተቋቋመው ኮሚቴ ለበዓሉ እያደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅትና በቀጣይ ባለን አጭር ጊዜ ሊተገበሩ የሚገቡ ጉዳዮችን በመለየት በጊዜ የለንም መንፈስ የዝግጅት ስራው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመግለፅ በቀጣይም በየ 5ቀኑ ንዑሳን ኮሚቴዎች የደረሱበትን ለአብይ ኮሚቴ እያቀረቡ እንደሚሄዱ በመግለፅ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል ።